እራሱ ለተሰበረ

የሐዲስ መጽሐፈ ፈውስ ገጽ 182፤ ቢኤል 828ቅ.73 ለአካላት ሁሉ እራሱ ለተሰበረ ተፈረስም ላይ ለወደቀ ተበቅሎም ለወደቀ እራሱም ላበጠ ለተገመሰ ላልተገመሰም ላላበጠም ደምም ታፉ ታፍንጫው ተዓይኑ ተጆሮው ላልፈሰሰው እንዴህ አድርገው ይፈውሱት አስቀድመህ እራሱን ላጨው የስንዴ[1] ፍትግ አሰር[2] የደቀቀ ዶቄት እስኪ ሆን ፍጨው የባቄላ[3] ዶቄት የምስር[4] ዶቄት የድምብላል[5] ፍሬ የአንስላል[6] ፍሬ የጥድ[7] ፍሬ ፲ቅንጣት የናትራን[8] ቅጠል ወቅጠህ... Continue Reading →

የሐረር ከተማ መወድስ

ይህ ባለ አራት ስንኝ የዓረብኛ ግጥም የሐረርን ከተማ ውበት ያወሳል፡፡ የከተማዋም ታላቅነት የተመሰረተው በቅዱሳኖቿ በአሚር ኑር ቢን ሙጀሃዲን እና ሼክ አባድር ጥበቃና በአዋቂዎቿ ብርሃን እንደሆነ ይናገራል፡፡

ጤናዳም

"እርጥበት እንደ ሙቀት ለበዛበት ሰው ፄና አዳም ደቁሰህ አጠጣው ወይም ቅጸሉን ይብላ"
1790

ሉቅዬ

ሉቅዬ (አማርኛ)፤ ፈሰሰት (ትግርኛ) Terpsiphone viridis (የሳይንስ ስም) መልክ ደረተ ነጭ፣ ዠርባቸው ቀይ ከለድማ፣ ቁንጯቸው ዝርዝር፣ ባለ ክበብ ዓይን አካለ ትንሽ ወፎች፤…. ቁመታቸው ከመንቆር እስከ ዥራት ጫፍ….ያኽላል። ወንዱ በክንፉ ጠርዝ ነጭ የጣለበት ሆኖ ከዥራቱ የሚቀጠሉ ረዥም ነጭ ላባዎች አሉት። መብል በራሪ ሕዋሳት ትዳር (ኑሮ) በጣም በረሃ ከሆኑ አከባቢዎች በስተቀር በመላ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።በበልግ (መጋቢት-ሰኔ) በባላ መጋጠሚያ... Continue Reading →

እንጀራ

በዚህ ዓለም ለብዙ ሥራ መፃር ምግብ ማዘጋጀት ተድላ ደስታ ማድረግ ምን ቁም ነገር አለው፤ በዚህ ዓለምስ የሚሻው ግማሽ እንጀራ ነው፡፡ ያም ባይሆን አንድ እንጀራ ነው፡፡ (መ.ብ. ወልደዮሐንስ 4)

ሰደቃ

ሰደቃ_ 18ኛ v የንጀራ ማቅረቢያ እግረ ረዥም ገበታ፣ መሶብ፣ አቆልቋይ፣ አውራጅ፤ ከስፌት፣ ከእንጨት የተበጀ፡፡ ኅብስት የሚያቀርቡበት ሰደቃ ነበራት፡፡ (ዕብራውያን 9.2 አንድምታ ገጽ 654) (ታሪክ) 19ኛ አጼ ቴዎድሮስ ጊምባ የሚባል ሀገርን ሊያስገቡ እኔ የክርስቶስ ባርያ የቅዱስ ዮሐንስ ዕለት እስላምና አማራን ባንድ ሰደቃ ያላበላሁ እደሆነ፤ ክርስቲያን አትበለኝ አሉ፡፡ እንዳሉትም ሆኖላቸው ባ1848 ዘመን መለወጫ ባንድ ሰደቃ ሁሉም በላ፡፡... Continue Reading →

ጥበብ

በዚህ ክፍል ያሉ ጽሑፎች ስለ ጥበብ የሚናገሩ ወይም በኪን የተሠሩ ሥራዎችን የሚዘግቡ ናቸው፡፡ ጥበብ የሚለው ቃል ትርጕሙ ብዙ ነው፡፡ በብሉይ አንድምታ ከአምላክ የሚገኝ ስጦታ፣ ለሰውነትም ለነፍስም የሚሆን መድኃኒት፣ ዕውቀት ተብሎ ተፈቷል፡፡ ከአንዳንድ ዘንድ ጥበብ ከዕውቀት ቢለይም በሌላ ቦታ ደግሞ ጥበብ እውቀትን፣ ምሳሌን፣ መዝሙርን (ግጥምን) አጠቃሎ ይገኛል፡፡ ይህን የትርጕም ልዩነት በማስተዋል ጥበብን በየመልኩ የሚገልጹ ምንባቦች ተመርጠዋል፡፡... Continue Reading →

Hello World!

Welcome to WordPress! This is your first post. Edit or delete it to take the first step in your blogging journey.

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑